ሁለተኛው የመጽሐፍ ግምገማ

መጽሐፉ – “ታሪክ የምትመሰክርልን . . .” ካሣ ገብረማርያም፤ ደራሲ – ስንታየሁ ካሣ

ግምገማ – በአቶ ዘነበ ኦላ (ጋዜጠኛና ደራሲ ናቸው።)

ሐምሌ 1 ቀን 2009 ዓ/ም በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል

4H5A4955
አቶ ዘነበ ኦላ

የዚህ መጽሐፍ ደራሲ ቤተሰቦች በዚህ መጽሐፍ ላይ አንብቤ አስተያየት እንድሰጥ ስለተጋበዝኩኝ ከልብ አመሰግናለሁኝ። ይህ መጽሐፍ በእርግጥ ከ48 ሰዓት ውስጥ ነው አእጄ የገባው። እኔ መጽሐፍ ገምጋሚ ነኝ – ለዚያውም ቀስ ብዬ ነው። 48 ሰዓት በቂ ጊዜ አልነበረኝም። በአጋጣሚ መብራቱ እየጠፋ፥እየሄድኩ፥ በበራ ቁጥር እየተነሳሁ፥ አቅሜ በፈቀደ መንገድ በወቅቱ መጽሐፉን ለዚህ አድርሼዋለሁ።

እዚህጋ በጣም ላመሰግናችሁ የምፈልጋችሁ ሰዎች አላችሁ። በአጋጣሚ ተሰባስባችኋል፣ ደስ ይላል። በቅርብ ጊዜ በአገራችን ላይ ሁላችሁም የየራሳችሁን ምስክርነት ለሰጣችሁ ሁሉ ያለኝን አክብሮት በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እፈልጋለሁ። ሁሉችሁንም ከልብ-ከልብ አመሰግናለሁ። የሠራችሁት ሥራ በአገራችን ሊመዘን ይችላል። አሪፍ ነው፤ ቀሺም ነው፣ ልክ ነው፣ ልክ አይደለም ሊባል ይችላል። ግን የተሰማችሁን ምስክርነታችሁን ያያችሁትን መጻፋችሁ ከሚገባው በላይ አንድ ደረጃ አስተሳሰባችን ማደጉን ይህ አጋጣሚ ያሳያል። ብንታደል ኖሮ እንደ ቪየትናም ብንሆን ደስ ይለኝ ነበር። ቪየትናም ከድሃው ታጋይ እስከ ሆ ቺ ሚኒ ድረስ ልምዳቸውን ጽፈው ከዚያ በኋላ ወደ ልማት ነው የገቡት። ሌሎችም ይህንን ቢያደርጉት ደስ ይለኛል። እዚህጋ የአንበሳውን ድርሻ የሚወስደው በቀድሞው አብዮታዊ ሠራዊት ውስጥ የምድር ጦር አባሎችን አሁንም ያለኝን ከፍተኛ አድናቆት በዚህ አጋጣሚ መግለጽ እፈልጋለሁ። ጽፋችኋል፤ ከዚህ በኋላም ጻፉ ብዬ ነው ተስፋ የማደርገው።

እዚህጋ የካሣ ገብረማርያም ሕይወት ልጃቸው ጽፋላቸዋለች። አንዳንድ ታሪክ ይካሄድና ያንን ታሪክ ስታነጻጽሩት የሚገርማችሁ አይነት ውጤት የምታገኙበት ጊዜ ኣለ። አሁን በቅርብ ጊዜ ታሪካችን ውስጥ ሕይወት ተፈራ የምትባል ልጅ ስለ ወንድ ጓደኛዋ (ቦይ ፍሬንድ) ስለ ጌታቸው ማሩ ጽፋለች። በእንግሊዝኛ ጽፋዋለች፤ ይኸውም ተተርጉሞ በአማርኛም ተጽፏል። ፍቅር ይኖራል፤ ለመጨረሻ ጊዜ ሊመክራት ሲሄድ አብረው አድረው፥ ተቀመጥ ስትለው “ጓደኞቼጋ ነውኮ የምሄደው” በሙሉ እምነት ብሎ ተሰነባብተው ሄዶ ነው የአረፈው። ይህች ልጅ ፍቅራቸው ለኔ ሰም ነው፤ ወርቁ የሱን ሕይወት ጽፋ ለጓዶቹ ምን ያህል ተሳስተው እንደነበረ ለምስክርነት ትልቅ ሃውልት አቁማለታለች።

ለኔ ስንታየሁ ልጅነቷ ሰሙ ነው፤ ወርቁ ጦር ግንባር እየሄደች ታይ ነበር፥ እያንዳንዱን ሥልጠና ታይ ነበር። በልጅ ዓይን ትመለከት ነበር። እነዚያ የአእምሮ ጓዳ ውስጥ ተቀምጠው ዛሬ ይሄ መጽሐፍ መሆን በቅቷል። ልብ አርጉ በእኛ አገር መረጃ ማግኘት ምን ያህል አስቸጋሪና ፈታኝ እንደሆነ ገምቱ፤ ያን ሁሉ ታግላ፥ የአባቷን የግል ማኅደር አግኝታ፥ እሳቸው ላይ ምስክርነት የሚሰጡ ሰዎች አግኝታ ለዚያ መሆን የሚገባውን ሀውልት፥ ጋሼ ሳህለሥላሴ እንዳለው አቁማላቸዋለችና ይሄ ሊደነቅ የሚገባው ነገር ነው። እዚህ መጽሐፍ ላይ ሳነብ የተሰማኝ ስሜት አንድ ነብስ ውስጥ ብዙ ነብሶች ናቸው የታዩኝ። አንድ ሰው ነብስ ውስጥ ኢንስትራክተር፥ መምህር፥ አሠልጣኝ እና የመዓት ጸጋዎች ባለቤት። ሕይወት አጭር ናት። ልብ እንድትሉ የሚያስፈልገው ነገር በዚህች 48 ዓመታት ጊዜ ሥር 6 ቆንጆ የሆኑ ልጆች፥ መልካም ትዳር፥ ዘራቸውን ትተው አንድ የሚያስወቅስ ጉዳይ ውስጥ ሳይገቡ አገራቸው በሰጠችው ድርጊት ላይ ተገቢውን ወታደራዊ ግዴታቸውን የተወጡ ሰው አይተናል። በ48 ዓመታት ውስጥ! ሕይወት አጭር ናት። ፀጋዬ ገብረመድህን ስለ ሼክስፒር ጉዳይ ተጠይቆ ሼክስፒር 52 ዓመቱ ነው፤ 52 ዓመት ነው የኖረው። 52 ዓመት አይደለም እንደዚህ ዓይነት ሥራ ለመሥራት የተሟላ ሳቅ እንኳን ለመሳቅ በቂ አይደለም ነው ያለው። የሚገርመው ነገር ኮሎኔል ኢንጆይ አርገዋል (በደንብ ተዝናንተዋል)። የዚያኑ ያህል ደግሞ በሚደንቅ መልኩ መሪ ፈጥረዋል። መሪ አሪፍ ነው፤ ቀሺም ነው በሌላ ጉዳይ የሚታይ ነው። መሪ ፈጥረዋል። ኮ/ል መንግስቱ ኃይለማርያምን አሠልጥነዋል። ኮ/ል ፍስሐ ደስታን አሠልጥነዋል። ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ሃብተማርያምን አሠልጥነዋል። ኮ/ል ተስፋዬ ወልደስላሴን አሠልጥነዋል። እነዚህ ሰዎች በቀድሞው ሥርዓት ውስጥ የነበራቸውን ቦታ በዓይነ ኅሊናችሁ ልታዩ ሞክሩ። እነዚህ ሰዎች ስለእኚህ ሰው የሚሰማቸውን እውነተኛውን ሰሜት ነው ለስንታየሁ ሊነግሯት የሞከሩት። እሷም ሚዛንዋን ጠብቃ በፍጹም ለአባትነት ያደለ በማይሆን መልኩ። ለዚያውም . . . እነዚህ ሰዎች ቦርን ሚሊታሪ ነበሩ። . . . ሌላው ቦርን ሚሊታሪ ተስፋዬ ሃብተማርያም ናቸው። ብ/ጄኔራል ተስፋዬ ምናልባት ከ2 እና 3 ዓመት በፊት መጽሐፍ ላይ ግምገማ ሲካሄድ፥ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቲ ውስጥ፥ “ሞተህ ብትነሳ እምትመረጠው ፕሮፌሽን ምንድነው?” ቢሉ “ውትድርና።” ነው ያሉት። እንደገና ወታደር መሆን ነው የሚፈልጉት። ነብሳቸው ለዚህ ጥሪ የሰጠ ነው። ይህን ጥሪ የተሟላ እንዲያደርጉ የኮ/ል ካሣ ገብረማርያም አሰልጣኝነት እጅግ ያስፈልጋቸው ነበር ማለት ነው። እንዲህ-እንዲህ እያልን ስንረዳ በሰዎች ነብስ ላይ አያልነቱ ተገልጿል። 6 ውብ ልጆች ተወልደዋል፥ ከልጆቻቸው መሃል አንድም አስወቃሽ የለም፥ ልትጽፍላቸው የሚገባት ልጅ ሰሙ እኮናት። ለእሳቸው ወርቁን ሰጥታናለችና እጅሽን ቁርጥማት አይንካው፣ ይቆይልኝ!

መጽሐፉን ባለ ጠንካራ ሽፋኑን (ሃርድ ከቨሩን) ያሳተመው ፀሐይ አሳታሚ ነው። በጣም ላመሰግነው እፈልጋለሁ። ምን ያህል አርክይቭ ቢከፍሉት ነው። ይህንን ጠጣር ሽፋን (ሃርድ ከቨር) ለእይታ ብቻ ብለው ነው የተውት። ገለጥ-ገለጥ አርጋችሁ እዩት። እንዴት ሊትረቸር፥ ስነ ጽሑፍን ፀሐይ አሳታሚ እንደሚያከብር ያሳያል። በእንደዚህ ያለ ጉልህ እና ግልጥ በሆነ ሥርዓት ነው ያስገባው እን ፀሐይ አሳታሚን ማመስገን እፈልጋለሁኝ።

ሁለት ጥቃቅን ስህተቶች ግን መጠቆም አለብኝ። አንደኛው ካፕሺን ስቶሪ ላይ እናቴ እገሌን እንጉዝ ሆና ትላለች፤ እርጉዝ ለእንስሳ እንጂ ለሰው አያገለግልም። እናቷ በዚያን ጊዜ ነብሰጡር ነበሩ። ሁለተኛው ሽምጥ ውጊያ ይላል – የቃላት ግድፈት መሰለኝ። ሽምጥ ውጊያ የሚባል ነገር የለም። የሽምቅ ውጊያ ነው – «ቅ» «ጥ» ሆና የቃላት ግድፈት ፈጠረች።

ያልተጠቀመችበት ዕድል ደግሞ ኮ/ል መንግሥቱ በጣም ጓግተው ነበር አግኝተዋት ሊያወጓት። በጣም እጅግ በጣም እንደሚያከብሯቸው እዚህ ላይ ያለውን ኢንተርቪው ስትመለከቱ የኮ/ል መንግሥቱ አክብሮት በካሣ ገብረማርያም ያለውን ፍቅርና አክብሮት ነው የምትመለከቱት። እና ሊያገኟት ሞክረው ነበር። እርግጠኛ ነኝ እኔ ስንታየሁ ከዚህ (ከመጽሐፉ) በላይ አክብራ የምታየው ነገር የለም። ሕይወቷን ሰጥታበታለች። ላለፈው 20 ዓመታት የታገለችበት ነው። ግን ብታገኛው ኖሮ ቴፕ ሬኮርደሩ ሲከፈት ያጠኑትን፥ ሊነግሯት የፈለጉትን ይነግሯታል። ከዚያ በኋላ ግን በጋዜጠኛ ቋንቋ ኦፍ ዘ ሬከርድ የሚባል አለ፣ ውባንቺ ምሳ አዘጋጅተው ቴፕ ሬከንደሩ ተዘግቶ መንግሥቱ ኃይለማርያም ከቅጂ ውጭ (ኦፍ አ ሬከርድ) ነግረዋት ምናልባትም ልናውቀው የሚገባንን ትልቅ ነገር ልታካፍለን ትችል ነበር። ዕድሉን አልፋዋለች። ብትችል መጽሐፉን ይዛላቸው ሄዳ ብታገኛቸው ለእሳቸውም ደግሞ ይዘሽላቸው ብትሄጂ ደስ የሚለኝ ሎንግ ኦፍ ፍሪደም የሚባል ነገር አለ ከሎንግ ኦፍ ፍሪደም ከኮምፕሌክስ ውጪ መጽሐፉ የት ያምራል? መንግሥቱ ኃይለማርያም ይማሩበታል። ይዘሽላቸው ሂጂ! የሰማነውን በልቦናችን ያሳድርልን።