ካሣ ገብረማርያም

colKassaGm
ኮሎኔል ካሣ ገብ,ረማርያም

ይህ ድረ-ገጽ ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያምን ለማስተዋወቅ፥ ለማስታወስና ለመዘከር ሲባል የቀረበ ነው። ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም በቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ሆነ በኮ/ል መንግሥቱ ኃይለማርያም አገዛዞች ወቅት ባገኟቸው የተለያዩ የጦር ሜዳ ድሎች በሠራዊቱ በጣም ስማቸው የገነነ የጦር መኮንን ነበሩ። በኢትዮጵያ ሕዝብ ግን ምንም ያህል አይታወቁም። በቀድሞ የጦር ኃይል አባላት የተጻፉ መጻሕፍት መውጣት ሲጀምሩ ነው የተዳፈነውና የተድበሰበሰው ገድላቸው ይፋ መውጣትና ለሕዝብ መገለጽ የጀመረው። አሁን ደግሞ ልጃቸው ዶ/ር ስንታየሁ ካሣ ብዙ ደክማና ጥራ የሕይወት ታሪካቸውን በመጻፍ ለንባብ አብቅታዋለችና የኢትዮጵያ ሕዝብ በይበልጥ እንዲያውቃቸው ይሆናል ብለን ተስፋ እናደርጋለን። ይህ ድረ-ገጽም ያንን ይረዳል። ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም በኤርትራ አንድነትን ለመጠበቅና ለማስከበር በተደረገው ፍልሚያ አንድ ግብረ ኃይል መርተው ብዙ ድል የተቀዳጁና ለወገን ጦር የድል ጎህ የቀደዱ ሲሆን፤ በመጨረሻም ናቅፋን ለማስለቀቅ በወጣው ዕቅድ በተሰጣቸው ልዩ ግዳጅ ጦራቸውን በእግር ጉዞ በመምራት በሳህል በረሃ በጠላት ወረዳ ሰንጥቀው ገብተው የድንገት ማጥቃት አደረጉ። በዚህም ግባቸውን በመያዝ የኤርትራውን ጦርነት ወሳኝ ደረጃ ላይ አድርሰው ግዳጃቸውን በድል ፈጸሙ። ሆኖም ጠላት ድጋፍ አግኝቶ እያየለ መጣ፤ እሳቸውም ይዞታቸውን አጥብቀው አልለቅም በማለት ፍልሚያውን ቀጠሉ። ከወገን በኩል አቅርቦት፥ ድጋፍና ደጀን ባለማግኘታቸው ጦራቸውም በውሃ ጥም ተፈታና ድሉም ተቀልብሶ በጠላት ሲከበቡ እስከ መጨረሻው ተዋግተው ለአገራቸውና ለወገናቸው እራሳቸውን በእራሳቸው በክብር መስዋዕት ያደረጉ የኢትዮጵያ የጦር መኮንን ናቸው። የኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም አጭር የሕይወት ታሪክን ለማንበብ ይህን ይጫኑ

ስለ መጽሐፉ አዘጋጀት

TP_Kassa_3D

ፀሐፊዋ የአባቷ የኮሎኔል ካሣ ገብረማርያምን ከልጅነት እስከ መጨረሻው ሕልፈታቸው ድረስ ያለውን ታሪካቸውን ለመጻፍ ከቤተሰብ፥ ከቅርብ ወዳጅና ጓደኞቻቸው፥ ከመጻሕፍት፥ መጽሔቶችና የመሳሰሉ ተጨባጭ መረጃዎች ሌላ ቁጥራቸው ከመቶ በላይ የሆነ , , , ካነጋገረቻቸውም ውስጥ ሶስት ባለፈው መንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣኖች፥ ጥቂት ሚንስትሮችና አምባሳድሮች የነበሩ፥ 10 ሜ/ጄኔራሎች፥ 17 ብ/ጄኔራሎች፥ 32 ኮሎኔልች፥ብዙ ሻለቆችና ሻምበሎች እና ጥቂት ሲቪሎችም ይገኙበታል።              ሙሉውን ለማንበብ ይህን ይጫኑ።

 

ፀሐፊዋ ዶ/ር ስንታየሁ ካሣ ከርዕዮት ዓለሙ የፀሐፊያን ድምጾች (ኢሳት) አዘጋጅ ጋር ያደረገችውን ቃለ -ምልልስ ያድምጡ፦

ክፍል 1            ክፍል 2

ፀሐፊዋ ዶ/ር ስንታየሁ ካሣ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ (VOA) የሰጠችውን ቃለ-ምልልስ ይህን በመጫን ያድምጡ።

ስለ መጽሐፉ አስተያየት

በአቶ ተረፈ ወርቁ ከሰንደቅ ጋዜጣ የተወሰደ

አስተያየት – በአቶ ታዬ ብርሃኑ

41ኛውን ዓመት ለማስታወስ የተዘጋጀውን ቪዲዮ ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

40ኛ ዓመት መታሰቢያ

IMG_0725 (3)
የክብር እንግዶቸ ብ/ጄኔራል ታዬ ጥላሁን አና ኮ/ል ስምረት መዳሃዬ ከመሃል ከጸሐፊዋ ግራና ቀኝ
5R8B9664
በዕለቱ የተገኙ የኢትዮጵያ አርበኞች ማኅበር አባላትና የኮ/ል ካሣ ገብረማርያም ቤተሰብ በከፊል

ሌሎች ፎቶግራፎችን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም የኢትዮጵያን ዳር ድንበር፥ ልዓላዊነትና አንድነት ለማስከበር ከዘውዱ አገዛዝ ጀምሮ ብዙ ግዳጆችንና ጦርነቶችን መርተው ለድል ማብቃታቸው ይታወቃል። በመጨረሻም በሰሜን፣ በሮራ ፀሊም ግዳጅ ላይ፣ ራሳቸውን በራሳቸው መስዋዕት አድርገዋል። የዚህን ዕለት 40ኛው ዓመት የመታሰቢያ በዓል ቅዳሜ ሐምሌ 13 ቀን 2011 ዓ/ም በጦር ኃይሎች መኮንኖች ክበብ፣ አዲስ አበባ፣ እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።  ይህንን በመጫን ንባቡን ይቀጥሉ

በኢሳት ዜና ላይ የቀረበውን ለመመልከት ይህንን ይጫኑ

የጀግና ሽልማት በዋሺንግተን ዲ ሲ 

Heroes Night DCየሰሜን አሜሪካ የጀግኖች በዓል አዘጋጅ ኮሚቴ በጳጉሜ 3 ቀን 2009 ዓ/ም በዋሺንግተን ዲሲ ባዘጋጀው እጅግ የደመቀ “የታላክ ኢትዮጵያውያን ጀግኖች ምሽት በዓል” ላይ ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም ለኢትዮጵያ አገራቸው አንድነትና ሉዓላዊነት በመዋደቅ ላበረከቱት የላቀ አስተዋጽኦ  ታላቅ ክብር፥ ምስጋናና አድናቆቱን ገልጾ “ለማይረሳ ውለታ” በሚል ርዕስ ጀግንነታቸውን የሚገልጽ የክብር ሽልማት አበርክቷል። ይህንንም ሽልማት ልጃቸው ዶ/ር ስንታየሁ ካሣ ትህትና በተሞላበት ክብርና ደስታ ተቀብላለች።

በዚህ ኮሚቴው ለአራተኛ ጊዜ በአዘጋጀው በዓል ላይ ሜ/ጄኔራል መስፍን ገብረቃል፥ ሜ/ጄኔራል መርዳሳ ሌሊሳ፥ ብ/ጄኔራል አሸናፊ ገብረፃዲቅ፥ ኮሎኔል ብርሃኑ ውብነህ፥ አምሳ አለቃ ገረመው ኃይለማርያም እና በምጽዋ ጦርነት በጀግንነት ለተሰውት የባህር ኃይል አባላት (በተወካይ) በተመሳሳይ ሁኔታ የጀግንነት ሽልማት በክብር ተበርክቶላቸዋል። ከዚህ በፊት እአአ 2008፥ 2009 እና 2010 ዓ/ም በተመሳሳይ ሁኔታ ሌሎች የሠራዊቱ አባላትን ኮሚቴው የሸለመ መሆኑ ይታወሳል።

ከደመቀው የሽልማቱ አሰጣጥ ስነ ስርዓት በኃላ የእያንዳንዱ ተሸላሚ ጀግና አጭር የሕይወት ታሪክ ተነቧል። ከዚያ የእራትና የመጠጥ ግብዣ ተካሂዶ የሙዚቃና የመዝናኛ ዝግጅቱ በመቀጠል በበዓሉ የተገኙትን ኢትዮጵያውያን በሙሉ በማስደሰት ተከናውኗል። በዚህም እኛ የተሰማንን ከፍተኛ ደስታና ክብር እየገለጽን አዘጋጅ ኮሚቴውንና በዓሉን እውን ለማደረግ ለጣሩት ሁሉ ያለንን አክብሮትና ምስጋና በትህትና እናቀርባለን።

ልዩ ዝግጅት በአዲስ አበባ ሂልተን ሆቴል

ከወራቶች በፊት ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያምን ለማስታወስና የመጽሐፍ ምረቃ ዝግጅቶች በአሜሪካን አገር 

4H5A4926
በአዲስ አበባው ዝግጅት ከተገኙት የቀድሞ ከፍተኛ ባለሥልጣኖች በከፊል

በቬሪጂኒያና በዳላስ ከተሞች መደረጋቸው ይታወሳል። የአዲስ አበባው ዝግጅት ለኮሎኔል ካሣ ገብረማርያም ቤተሰብ፥ የቅርብ ዘመድና ወዳጅ ሁሉ በብዙ መልኩ የተለየ ነበር። ከሁሉም በላይ እራሳቸውን ለወገንና አገር በሰውበት ምድር፥ በኢትዮጵያ፥ መታወሳቸውና የሕይወት ታሪካቸውም ለሕዝብ ለንባብ መብቃቱ እጅግ የሚያረካ በመሆኑ ነው። ስለሆነም ይህ ዝግጅት ከቤተሰብም ውጭ በብዙ ሰዎች በናፍቆትና በጉጉት ይጠበቅ የነበር ነው።  ይህንን በመጫን ንባቡን ይቀጥሉ

0Y1A9003
በአዲስ አበባው ዝግጅት ደራሲዋ ከቀድሞ የትምህርት ጓደኞቿ ጋር።

የአዲስ አበባውን ዝግጅት ሌሎች ፎቶግራፎች ለመመልከት ይህን ይጫኑ

የመጽሐፍ ግምገማ፦

በዚህ ዝግጅት የቀረቡትን የመጽሐፉ ግምገማዎች ከዚህ በታች ያሉትን በመጫን ያንብቡ፦

የዶ/ር ሳህለ ሥላሴ ብርሃነ ማርያም የመጽሐፉ ግምገማ        የአቶ ዘነበ ኦላ የመጽሐፉ ግምገማ

 መጽሐፉን ለማግኘት፦

የመጽሐፉ ርዕስ ፦ታሪክ የምትመሰክርልን . . . ’ ካሣ ገብረማርያም  ሲሆን  ደራሲዋ ስንታየሁ ካሣ ነች።

መጽሐፍን ከአማዞን ለማግኘት ይህን ይጫኑ።

ወይም በPayPal በዴቢት ወይም ክረዲት ካርድ መጽሐፉን ለማግኘት ቀጥሎ ያለውን ይጫኑ።

 

Buy Now Button with Credit Cards

de_1044
ከዳላስ ዝግጅት

የዳላስቴክሳስ ልዩ ዝግጅት  (04/04/2017)

ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያምን ለማስታወሰና መጽሐፉን ለመመረቅ የዳላስ ቴክሳስን ዝግጅት በአጭር ጊዜ በመሰባሰብ የተሳካ እንዲሆን ለረዱን . . .  በበዓሉ ተገኝተው አብረውን ላከበሩት ሁሉ እጅግ የላቀ ምስጋናችንን በትህትና እንገልጻለን።

የዳላስ ዝግጅትን አጭር ሪፓርት ለማንበብ ይህን ይጫኑ።

ልዩ ዝግጅት በቨርጅኒያ!

ve_0170
ጸሐፊዋ መጽሐፍ በመፈረም ላይ።

ቅዳሜ ማርች 18 ቀን 2017 በቨርጂንያ በሚገኘው በመዓዛ ሬስቶራንት ጀግናው ኮሎኔል ካሣ ገብረማርያምን ለማስታወስና በልጃቸው በዶ/ር ስንታየሁ ካሣ የተጻፈው የሕይወት ታሪካቸውን የሚተርከው መጽሐፍ ምረቃ ልዩ ዝግጅት ከሶስት መቶ ሰው በላይ በተገኘበት እጅግ በደመቀ ሁኔታ ተከብሯል።

ስለ ዝግጅቱ አከባበር በኮሚቴው የቀረበውን ዘገባ ለማንበብ ይህን ይጫኑ።